የሌማት ትሩፋት መርሃግብር ለማሳካት ያለመ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

296

አዳማ( ኢዜአ) ህዳር 21/2015 የሌማት ትሩፋት መርሃግብር ለማሳካት ያለመ የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል ።

መድረኩ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴንን ጨምሮ የክልሉ የግብርና ቢሮ ሃላፊዎች የሴክተሩ የስራ ሃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ ሀገራዊ የሌማት ቱሩፋት ዕቅድ በሚኒስቴሩ የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ ቀርቧል ።

በተለይ የሌማት ቱሩፋት መርሃግብሩን ለማሳካት በስንዴ፣ ሩዝ፣ የወተት ላሞች፣ የስጋና እንቁላል ዶሮ ፣ በዓሣ ሀብት ፣ በማር ልማት ፣ የግመል በጎችንና ፍየሎችን ዝሪያዎችን ከማሻሻል ጀምሮ የሀብት ልማቱን ማዘመን የሚቻልበትን ዝርዝር የማስፈፀሚያ ስልቶችን የያዘ ዕቅድ መሆኑን ገልጿል ።

በዚህም አሁን የሰብል፣ የእንስሳትና የአሳ ሀብት ልማት ላይ የሚታዩ ኋላቀር የአመራረት ዘይቤን ከመቀየር ጀምሮ ዘመናዊና የተሻሻሉ ዝሪያዎችን ወደ ልማቱ ለማስገባት ይሰራል ተብሏል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም