ዲፕሎማቶች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ በብልሀት የሚመራ የዲፕሎማሲ ሥራ ሊያከናውኑ ይገባል—አቶ ደመቀ መኮንን

451

አዲስ አበባ ህዳር 18 ቀን 2015 (ኢዜአ) ዲፕሎማቶች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ወቅቱን ያገናዘበና በብልሀት የሚመራ የዲፕሎማሲ ሥራ ሊያከናውኑ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳሰቡ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዋና መስሪያ ቤትና በተለያዩ አገራት ኢትዮጵያን ወክለው ለሚሰሩ ዲፕሎማቶች በአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል ።

May be an image of 13 people, people sitting, people standing, suit and indoor

በመዝጊያ መርሃ ግብሩ የተገኙት አቶ ደመቀ መኮንን በዚሁ ወቅት፤ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ዲፕሎማቶች ወቅቱን ያገናዘበ፣ በብልሀት የሚመራ የዲፕሎማሲ ሥራ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ስልጠናው ዲፕሎማቶቹ አሁናዊ የሆነውን ተለዋዋጭ፣ ተገማች ያልሆነውን እና የተወሳሰበውን የዓለም ስርዓት በማንበብ የሀገራቸውን እውነት እና ጥቅም ማስከበር እንዲችሉ የሚያግዝ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ስልጠናው የተሰጠውን አገራዊ ተልዕኮ በብቃት የሚያከናውን ዲፕሎማት ለመፍጠርም ሰፊ ጠቀሜታ ያለው መሆኑንም ገልጸዋል።

በማጠናቀቂያ ስነስርዓቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋዬ ይልማ የተገኙ ሲሆን ለሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።

በስልጠናውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ስልጠና መስጠታቸው እና ልምዳቸውን ማካፈላቸውም ይታወቃል፡፡