ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ በትብብር እንደሚሰሩ አስታወቁ

171

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 17 ቀን 2015 ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን በሰላም እና ፀጥታ ዙሪያ በትብብር እንደሚሰሩ አስታወቁ።

ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን በሌሎች ዘርፎች ተባብረው እንደሚሰሩ ሁሉ በሰላምና ደህንነት ጉዳይም ተባብረው መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ ሌተናል ጄኔራል ማርሻል ስቴፈን ባባነን ገልጸዋል።

ዛሬ የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የመረጃ ጀነራል መኮንኖች በሠላም እና ፀጥታ ዙሪያ በጋራ መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በአዲስ አበባ ተወያይተዋል፡፡


የደቡብ ሱዳን መከላከያ ሠራዊት ወታደራዊ መረጃ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል ማርሻል ስቴፈን ባባነን በዚሁ ወቅት እንዳሉት ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የሁለቱን ሀገራት ሰላም ለማረጋገጥ፤ የአካባቢ ደህንነትን በጋራ ለመጠበቅ እየሠሩ መምጣታቸውን ገልፀው አሁን ላይም በሠላም እና በፀጥታ ዙሪያ በጋራ ይሠራሉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡


በኢፌዴሪ መከለከያ መረጃ ዋና መምሪያ በኩል ደግሞ ሜጄር ጀነራል ደምሰው አመኑ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን በሁሉም መሥክ በትብብር የመሥራት ታሪክ ያላቸው መሆኑን ጠቁመው ወደፊትም ደህንነትን ለማስጠበቅ በፀጥታ ዙሪያ በጋራ መሥራቱ አስፈላጊም ተመራጭም ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡


የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን ህዝብ የቆዬ ታሪክ፣ ባህል እና ወግ ተጋሪዎች በመሆናቸው ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ የህዝቦች ተጠቃሚነት ለመቀየር ሰላምና ደህንነት ወሳኝ በመሆኑ የተጠናከረ የመረጃ ልውውጥ መኖር እንዳለበት መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም