የቻይና ኤምባሲ የአዲስ አበባ ከተማን የአገልግሎት አሰጣጥ የሚያሻሽሉ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች አበረከተ

114

አዲስ አበባ /ኢዜአ/ ህዳር 12/2015 /የቻይና ኤምባሲ የአዲስ አበባ ከተማን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የሚረዱ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ ።

የቻይና ኤምባሲ የከተማ አስተዳደሩን የአገልግሎት አሰጣጥ የሚያሻሽሉ ድጋፎች ማድረጉ የአገልግሎት አሰጣጡን እንደሚያቀላጥፈው የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻችው አስፍረዋል ።

በዚህም “የከተማ አስተዳደራችን የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማሻሻል በሚያደርገው ጥረት የቻይና ኤምባሲ አሰራሩን የሚያጠናክሩ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እና የአገልግሎት ቁሳቁሶችን ድጋፍ ስላደረገልን እናመሰግናለን” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም