ታላቁ ሩጫ ለከተማችን ከስፖርታዊ ውድድርነቱ ባሻገር የአብሮነት፣ የሰላምና የፍቅር እንዲሁም የትብብር ተምሳሌት ጭምር ነው-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

191

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 11 ቀን 2015 ታላቁ ሩጫ ለከተማችን ከስፖርታዊ ውድድርነቱ ባሻገር የአብሮነት፣ የሰላምና የፍቅር እንዲሁም የትብብር ተምሳሌት ጭምር ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።

ከንቲባ አዳነች የከተማችን ድምቀትና ውበት የሆነው የ2015 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር አስጀምረናል ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመልዕክታቸውም አብረን ስንሆን እናምራለን፤ ኢትዮጵያችንም ከፍ ትላለች ብለዋል።

ታላቁ ሩጫ ለከተማችን ከስፖርታዊ ውድድርነቱም ባሻገር የአብሮነት፣ የሰላምና የፍቅር እንዲሁም የትብብር ተምሳሌት ጭምር ነውም ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለውድድሩ አዘጋጆች፣ ተሳታፊዎችና አሸናፊ ለሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ የሚል የደስታ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም