የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት አደጋ ሳያደርሱ ረጅም ጊዜ ላሽከረከሩ 290 የተቋሙ አሽከርካሪዎች እውቅና ሰጠ

183

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 10/2015የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት አደጋ ሳያደርሱ ረጅም ጊዜ ላሽከረከሩ 290 የተቋሙ አሽከርካሪዎች እውቅና ሰጠ፡፡

በዚሁ የእውቅና መርሃ-ግብር ላይ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍሬህይወት ትልቁ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ9ኛ ጊዜ በተካሄደው የኢትዮጵያ የጥራት ሽልማት ላይ ድርጅቱ ሶስተኛ እንዲወጣ ላስቻሉ አሽከርካሪዎች እና ሰራተኞች ክብር ይገባቸዋል ብለዋል።

ድርጀቱ የ "ዜሮ አደጋ" መርሃ ግብር ተግባራዊ በማድረግና አደጋን ተከላክሎ በማሽከርከር ህበረተሰቡን የመጠበቅ ሀላፊነቱን በተግባር በመወጣት ላይ ነው ብለዋል፡፡

የአገር ሀብትን ከውድመት ለመጠበቅ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

በመርሃ-ግብሩ ላይ በ2014 ምንም አይነት አደጋ ሳያደርሱ ላጠናቀቁ 290 የአውቶብስ አሽከርካሪዎች እውቅና ሠጥቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም