የጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ ለአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት 5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አደረገ

139

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 9 ቀን 2015 የጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ ለአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት 5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሴ እና ልዑካቸው ጋር ተወያይተዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከውይይቱ በኋላ በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት በከተማችን እየተካሄደ በሚገኘው የወንዝ ዳርቻ ልማት ጉዳይ ከአምባሳደሩና ከልዑካቸው ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል በለዋል።

በውይይታቸው ላይ ከወንዝ ዳር ልማቱ በተጨማሪ በመለስተኛ የመጫወቻ ሜዳዎች ልማት እና በባህል ልውውጥ ዙርያ አብሮ ለመስራት መስማማታቸውን ገልጸዋል፡፡ከንቲባ አዳነች የጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ ለወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ላበረከተው የ5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም