የ30 አመት የተቀናጀ የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ማስተር ፕላን ይፋ ሆነ

154

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 1/2015 የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የትራንስፖርት መሠረተ ልማት የ30 አመት የተቀናጀ ማስተር ፕላን ይፋ አደረገ።

የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ እንደገለጹት ብሄራዊ የሎጅስቲክስ ፖሊሲ ለቀጠናዊ ትስስሩ ያለውን ሚና ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ ነው።

ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው በተለይ የትራንስፖርት ዘርፉን በማዘመን ኢትዮጵያን የቀጠናው ዋንኛ የሎጅስቲክስ መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

ይህንንም ለማሳካት ሚኒስቴሩ የ30 አመት የተቀናጀ የትራንስፖርት ማስተር ፕላን ተግባራዊ ለማድረግ ወደ ስራ መግባቱን አንስተዋል።

ማስተር ፕላኑ ከዓለም አቀፍ ልምድ በመነሳት እያንዳንዱን የትራንስፓርት እድልና ተግዳሮት የሚመለከት እንደሆነ ተመላክቷል።

ማስተር ፕላኑ እውን እንዲሆን የግሉ ዘርፍና የልማት አጋሮች በስፋት እንደተሳተፉበት ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም