የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪው ደቡብ ሱዳናዊ በሃገራቸው በመስኖና ውሃ ሃብት ሚኒስትርነት ተሾሙ

647

ጥቅምት 29/2015(ኢዜአ) በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በመከታተል ላይ ያሉት ደቡብ ሱዳናዊ በሃገራቸው የመስኖ እና የውኃ ኃብት ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ።

የደቡብ ሱዳን ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ትናንት ማምሻውን ይፋ ባደረገው ዘገባ ፓል ማዊ ዴንግ የመስኖ እና የውኃ ኃብት ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ በፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት ተሹመዋል።

ቀደም ሲል የደቡብ ሱዳን የመስኖ እና የውኃ ኃብት ሚኒስትር ሆነው ሲያገልገሉ የነበሩት ማናዋ ፒተር ጋትኩኦት ባለፈው ሰኔ ግብጽ መዲና ካይሮ ውስጥ ከልብ ህመም ጋር በተያያዘ ያልተጠበቀ ህልፈታቸው መሰማቱ የሚታወስ ነው።

ፓል ማይ ዴንግ በኢትዮጵያ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ መሆናቸውን ከዩኒቨርሲቲው የተገኘ መረጃ ያስረዳል።

አዲሱ የፓል ማይ ዴንግ ሹመት ማናዋ ፒተር ጋትኩኦት ህልፈት ከተሰማ ከአምስት ወር በኋላ የተሰጠ መሆኑን የደቡብ ሱዳን ምንጮች ይፋ አድርገዋል።

ፖል ማዊ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውንም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን ማጠናቀቃቸው ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም