የአየር ንብረት ለውጥ ተጽኖን ለመከላከል ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ ወዳጅነት ስምምነት አሳቤ ተፈጻሚ እንዲሆን ማድረግ አለባቸው-አንቶኒዮ ጉተሬዝ

739

አዲስ አበባ ኢዜአ ጥቅምት 28/2015 የአየር ንብረት ለውጥ ተጽኖዎችን ለመከላከልና ለመቀነስ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ ወዳጅነት ስምምነት እሳቤን ተፈጻሚ ማድረግ አለባቸው ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ተናገሩ።

በግብጽ ሻርም አል ሼክ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን 27ኛውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንበረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ-27) መክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ዋና ጸሐፊው "በሚቀጥሉት10 ዓመታት አለማችን ከፍተኛ በሆነ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽኖዎች ውስጥ ታልፋለች" ብለዋል።

"የአየር ንብረት ለውጥ ተጽኖንን በትብብር መግታት ካልተቻለ የሰው ልጆች ሲኦላማ ወደ ሆነ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽኖ ጎዳና ማምራታቸው አይቀሬ ነው" ሲሉ አሳስበዋል።

አለማችን በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ውስጥ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽኖዎችን ማሸነፍ ወይ መሸነፍ አማራጮች ውስጥ ታልፋለች ብለዋል።

ሀገራት ሁለት አማራጮች አሏቸው ያሉት ዋና ጸሐፊው ታሪካዊ የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽኖ የወዳጅነት ስምምነት እሳቤን ተግባራዊ በማድረግ የበካይ ጋዝ ልቀትን በመቀነስ የካርበን ልቀትን ዝቅ ለማድረግ ወይም አለማችንን ከፍተኛ ለሆነ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽኖዎች ለመዳረግ አማራጭ አላቸው ሲሉ ተናግረዋል።

አለም የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ፣ንጹህ ሃይልን በማመንጨት ዝቅተኛ የካርበን ልቀት ቴክኖሎጂን ለማረጋገጥ እድሎች አሏት ያሉት ዋና ጸሐፊው የአየር ንብረት ለውጥ ትግሉ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ ውደ አሸናፊነት እንዲያድግ ሀገራት ለወዳጅነት ስምምነቱ እሳቤ መተግበር መስራት አለባቸው ብለዋል።

በግብጽ በመካሄድ ላይ በሚገኘው 27ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

ትናንት በሻርም አል ሼክ ከተማ የተጀመረው 27ኛው የአየር ንብረት ጉባኤ እስከ ሕዳር 9 ቀን 2015 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ከ190 አገራት ይሳተፉበታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም