ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ጎን ለጎን ከበርካታ መሪዎች ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

108

ጥቅምት 28/2015 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ጎን ለጎን ከበርካታ ሃገራት መሪዎች ጋር መወያየታቸውን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው “ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ጎን ለጎን፣ ከበርካታ ሀገራት መሪዎች ጋር በሁለትዮሽ እና ስልታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል” ብለዋል።

“በተጨማሪም፣ ከአህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ጋር በጋራ የትኩረት ጉዳዮች ላይ ተወያይቻለሁ” በማለት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም