የሰላም የስምምነቱ ለኢትዮጵያ ሰላምና ብልጽግና መሰረት ይጥላል - ሩሲያ

267

ጥቅምት 24 2015 (ኢዜአ ) ሩሲያ የፌደራል መንግስትና ሕወሓት የተፈራረሙት የሰላም ስምምነት ለኢትዮጵያ ሰላምና ብልጽግና መሰረት እንደሚጥል ገለጸች።

ስምምነቱ ኢትዮጵያውያን እርቅ እንዲፈጥሩ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል ብላለች።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ በፌደራል መንግስትና ሕወሓት መካከል የተፈረመው ስምምነት የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ለማቋቋምና ለመላው ኢትዮጵያውያን ሰላምን አረጋጥጠው ብልጽግናን እንዲያገኙ ጠንካራ መሰረት የሚጥል እንደሆነ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም