የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር ማኪ ሳል መንግስትና ሕወሓት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉ እንደሚያበረታቱ ገለጹ

119

ጥቅምት 24 ቀን 2015 (ኢዜአ) የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበርና የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል የኢፌዴሪ መንግስትና ሕወሓት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉ እንደሚያበረታቱ ገለጹ።

ማኪ ሳል የሰላም ስምምነት ለተፈራረሙት ወገኖች ያላቸውን አድናቆት በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ስምምነቱ በጣም አስደሳች ዜና ነው ያሉት ሊቀመንበሩ ሁለቱን ወገኖች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል።

መንግስትና ሕወሓት ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የጀመሩትን እንቅስቃሴ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም