በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት ለተደረሰው የሰላም ስምምነት ስኬት አሜሪካ ድጋፏን ትቀጥላለች

151

ጥቅምት 24 ቀን 2015 (ኢዜአ) የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ሲካሔድ የቆየው የኢፌዴሪ መንግስትና ህወሃት የሰላም ውይይት በስኬት በመጠናቀቁ አድናቆታቸውን ገለጹ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የውይይቱን በሰላም መጠናቀቅ ተከትሎ ከደቡብ አፍሪካ የአለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር ጋር መነጋገራቸውን ገልጸው አቡብ አፍሪካ ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር ይሄንን መድረክ በማመቻቸቷ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የጦር መሳሪያ ድምጹችን በማስቆም የሰብዓዊ እርዳታና መልሶ መቋቋም ስራውን ለማከናወን በሚደረገው ቀጣይ ስራም ከአፍሪካ ህብረት ጎን በመሆን አሜሪካ ድጋፏን እንደምታጠናክር ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ መንግስትና በህወሃት መካከል የተካሔደው የሰላም ስምምነት ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱንና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ባስከበረ መልኩ ትላንት መጠናቀቁ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም