"አሸባሪው ህወሃት በአመለካከት ያልተቀበሉትን መግደል፣ ማሳደድ እና ማሰር መለያ ባህሪው ነው" -አቶ መልካሙ ሹምየ

81

ጥቅምት 23/2015 (ኢዜአ) "አሸባሪው ህወሃት በአመለካከት ያልተቀበሉትን መግደል፣ ማሳደድ እና ማሰር መለያ ባህሪው ነው" ሲሉ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበር አቶ መልካሙ ሹምየ ተናገሩ፡፡

አቶ መልካሙ አሸባሪው ህወሃት ለ17 ዓመታት የትጥቅ ትግል ያካሔድኩት ዴሞክራሲን ለማምጣት ነው ይበል እንጂ ዴሞክራሲን ቃሉን ከመናገር ባለፈ በተግባር የማያውቅ ፍጹም አምባገነን ቡድን  ነው ብለዋል፡፡

ገና ከጥንስሱ ጀምሮ በሃሳብ የማይመሳሰሉትን እየረሸነ እና እየሰወረ የመጣ ቡድን መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ምክትል ሊቀመንበሩ "ቡድኑ ለስልጣኑ ስጋት መስለው የታዩ ዜጎችን ሁሉ ከመግደል፣ ከማሳደድ እና ከማሰር ውጭ የሆነ ታሪክ የለውም" ብለዋል፡፡

አቶ መልካሙ አክለውም የሽብር ቡድኑ በትጥቅ ትግሉ ወቅት የተለየ ሃሳብ ያላቸው አመራሮችን ለውይይት ጠርቶ መረሸኑን አውስተው፤ ይህም ቡድኑ ሲፈጠር ጀምሮ ጨካኝ እና አምባገነን መሆኑን ያሳያል ነው ያሉት፡፡

የሽብር ቡድኑ በኢትዮጵያ መንበረ ስልጣኑን ተቆጣጠሮ በገዛባቸው 27 ዓመታት ያልፈጸመው ግፍ እንደሌለ በማንሳት፤ በሰሜን እዝ ላይ የፈጸመው ጥቃትም የቡድኑ እኩይነት ምን ያሀል የከፋ መሆኑን ማረጋገጫ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የሽብር ቡድኑ ባሉት ሁለት ዓመታት በፈጸማቸው ወረራዎችም በአማራና በአፋር ክልል መጠነ ሰፊ የሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት አድርሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም