"የነገዋ ኢትዮጵያ የተሻለች እንድትሆን የተሻለ ትውልድ እያፈራን እንቀጥላለን"-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ - ኢዜአ አማርኛ
"የነገዋ ኢትዮጵያ የተሻለች እንድትሆን የተሻለ ትውልድ እያፈራን እንቀጥላለን"-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
137
ጥቅምት 20/2015 (ኢዜአ) "የነገዋ ኢትዮጵያ የተሻለች እንድትሆን የተሻለ ትውልድ እያፈራን እንቀጥላለን" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።
የወዳጅነት ፓርክ ሁለተኛው ምዕራፍ ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉን አብስረዋል።
ፓርኩ ስፖርትን፣ ጨዋታንና ማኅበራዊ መስተጋብርን ያቀናጀ መሆኑን አስረድተዋል። ልጆች እየተጫወቱ ሳይንስና ቴክኖሎጂን ይለማመዳሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርኩ ወጣቶች ያነብባሉ፣ ስፖርትም ይሰሩበታል ነው ያሉት።
ወላጆችና አያቶች ከልጆቻቸው ጋር መጥተው ማኅበራዊ ልምዳቸውን ይለዋወጡበታል ብለዋል።
አዲስ ተጋቢዎች በሠርግ ዐጸዱ ጋብቻቸውን ይመሠርታሉ ሲሉም ጠቅሰዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የነገዋ ኢትዮጵያ የተሻለች እንድትሆን የተሻለ ትውልድ እያፈራን እንቀጥላለን ሲሉ ነው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ያስታወቁት ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ቁጥር ሁለት ወዳጅነት አደባባይን ዛሬ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ማድረጋቸው ይታወቃል።