ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፤ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ የበጋ መስኖ እርሻ ስራዎችን ጎበኙ

303

ጥቅምት 19 ቀን 2015 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፤ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ በመገኘት የበጋ መስኖ እርሻ ስራዎችን ጎበኙ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው በወረዳው ቆቃ ነጋዎ ቀበሌ አርሶ አደሮች አያከናወኑ ያሉትን የበጋ መስኖ ስንዴ እርሻ ተመልክተዋል።

በወረዳው ከ21 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበጋ መስኖ የማልማት ስራ ተጀምሯል።

በዘንድሮ ዓመት በአገር አቀፍ ደረጃ በበጋ መስኖ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በስንዴ ሰብል የመሸፈን እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑም ይታወቃል።

በዚህም በበጋ መስኖ ብቻ 52 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ የማምረት እቅድ መያዙን ከግብርና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።