የትራንስፖርት ባለስልጣን 18 ዓይነት የአገልግሎቶችን በኢንተርኔት መስጠት ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የትራንስፖርት ባለስልጣን 18 ዓይነት የአገልግሎቶችን በኢንተርኔት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ መስከረም 15/2011 የትራንስፖርት ባለስልጣን 18 የአግልግሎት አይነቶችን በኢንተርኔት መስጠት ጀመረ። ባለስልጣኑ ዛሬ ከመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ይህን አዲስ አገልግሎት መስጫ መንገድ ይፋ አድርገዋል። አገልግሎቱ ሶስት ዘርፎችን የሚያካትት ሲሆን እነርሱም የተሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ ፣ የጭነት ትራንስፖርትና የህዝብ ትራንስፖርት ናቸው። አገልግሎቱን ማንኛውም ደንበኛ ባለበት ሆኖ ኦንላይን ላይ የተዘጋጀ ፎርም በመሙላት መጠቀም የሚቻል ሲሆን ይህም ጊዜና ገንዘብ ለመቆጠብ እንግልትና የሙስና ተጋላጭነትን ለመቀነስ ታስቦ መሰራቱ ተጠቁሟል። www.eservices.gov.et ብሎ በመግባት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይቻላል።