የኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የውሃ ሚኒስትሮች በታላቁ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል ላይ ውይይት ጀመሩ

72
አዲስ አበባ መስከረም 15/2011 የኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የውሃ ሚኒስትሮች በታላቁ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል ዙሪያ አዲስ አበባ ላይ ውይይት ጀምረዋል። ውይይቱ የተጀመረው የሶስቱ አገራት መሪዎች በቤጂንጉ የቻይና-አፍሪካ ፎረም ላይ ባካሄዱት የሶስትዮሽ ውይይት ባሳለፉት ውሳኔ መሰረት ነው። የውሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፣ የግብጹ አቻቸው ዶክተር ኢንጂነር አብደል አቲ እና የሱዳኑ የውሃ ሃብት መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር ኢንጂነር ከድር ቀሰም አሰይድ ናቸው ውይይቱን የጀመሩት። ባለፈው ግንቦት በአዲስ አበባ በተካሄደው የመሪዎችና ሚኒስትሮች ውይይት የውሃ አሞላሉን የሚመረምር ሳይንቲስቶችን ያቀፈ ኮሚቴ ተቋቁሞ ስራ መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን የዛሬው ውይይትም የኮሚቴውን የምርመራ ውጤት አድምጦ ይመክራል ተብሏል። ኮሚቴው ስራውን በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥም ለማወቅ ተችሏል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም