ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ የሻሸመኔን የገጠር ሽግግር ማዕከል እየጎበኙ ነው

1136

ሻሸመኔ መስከረም 13/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድ የሻሸመኔን የገጠር ሽግግር ማዕከል እየጎበኙ ነው።

በአስር ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፈው የማዕከሉ ግንባታ የተጀመረው በየካቲት 2010 ዓ.ም ሲሆን ከሁለት ወራት በኋላ ይጠናቀቃል ተብሏል።

በአሁኑ ወቅት የግንባታው 60 በመቶ ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን 400 ሠራተኞችም አሉት።

ማዕከሉ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ማር፣ ወተትና የወተት ተዋጽኦ፣ ዶሮና እንቁላል እንዲሁም ሌሎች የግብርና ውጤቶችን ለቡልቡላ ኢንተግሬትድ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ በግብዓትነት ያቀርባል።