የመውሊድ በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች እየተከበረ ነው

211

መስከረም 28/2015 (ኢዜአ) 1 ሺህ 497ኛው የመውሊድ በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ በአዲስ አበባ በታላቁ አንዋር መስጂድ የሃይማኖት አባቶች፣ የእምነቱ ተከታዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ከማለዳው ጀምሮ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች በመከበር ላይ ነው።

በአንዋር መስጂድ እየተከበረ ያለውን በዓል የታላቁ አንዋር መስጂድ ኢማም ሸህ ጣኻ ሀሩር ቁርአን በመቅራትና ዱዓ በማድረግ አስጀምረዋል።

የመውሊድ በዓል በነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) መልካም ተግባራትን የህይወት መርህ ለማድረግ በማሰብ የሚከበር በዓል ነው።

የሰላም፣ የፍትሕ፣ የበጎነትና የአንድነት ፈለጋቸውን መከተል እንደሚገባም ተነግሯል።

በዓሉን በማስመልከት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ዛሬ ማለዳ ዘጠኝ ጊዜ መድፍ ተኩሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም