የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ፈተናውን ወደ ሚወስዱበት ዩኒቨርስቲ እየገቡ ነው

427

መስከረም 26 /2015 (ኢዜአ) የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ፈተናውን ወደ ሚወስዱባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እየገቡ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፈተናውን በዩኒቨርሲቲዎች ለመስጠት በቂ ዝግጅት መረጉን የገለጹ ሲሆን የፈተና መስጫና የመኝታ ክፍሎች ዝግጅት፣ የፀጥታና ደህንነት ዝግጅት አመርቂ መሆኑንም አመላክተዋል።

ከመስከረም 30/2015 ጀምሮ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከ975 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።