ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው በፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ከሚመራው የኬንያ ሪፐብሊክ ልዑካን ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው በፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ከሚመራው የኬንያ ሪፐብሊክ ልዑካን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ መስከረም 26/ 2015 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው በፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ከሚመራው የኬንያ ሪፐብሊክ ልዑካን ቡድን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

በኢትዮጵያ እና በኬንያ መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ሁለቱ መሪዎች መናገራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ አመልክቷል።
ኢትዮጵያ እና ኬኒያ ጋር ለረዥም ጊዜ የዘለቀ ወዳጅነት እና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረት ትብብር ያላቸው አገራት ናቸው።