ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በሰላም መጡ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

258

መስከረም 26 ቀን 2015 (ኢዜአ) “ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በሰላም መጡ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መልካም ምኞታቸውን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቲውተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት የኬንያና የኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ጥብቅ ወዳጅነት ትኩረት በማድረግ በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ መሆኑን ገልጸዋል።

የኬንያው አዲሱ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኢትዮጵያ መግባታቸውና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤