በጣሊያን የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸነፉ

321

መስከረም 22 /2015 (ኢዜአ) በጣሊያን ትሬንቶ በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል።

በውድድሩ በወንዶች የዓለም ሻምፒዮኑ ታምራት ቶላ የቦታውን ሰዓት በማሻሻል ሲያሸንፍ በሴቶች ደግሞ ብሩክታይት ደገፋው ድል ቀንቷታል።

በወንዶች 10 ኪሎ ሜትር ውድድርም እንዲሁ ሙክታር ኢድሪስ ማሸነፉን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል።