በጋምቤላ በጎርፍ የተጎዱ አካባቢዎችን ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እየጎበኙ ነው

104

ጋምቤላ መስከረም 22/2015 (ኢዜአ) በጋምቤላ ክልል በጎርፍ ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎችን የክልሉና የፌደራል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እየጎበኙ ነው።

በመስክ ምልከታው የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድ፣ የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ዶክተር ሽፈራሁ ተክለማርያምን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሀላፊዎች ተሳትፈዋል።

የስራ ሀላፊዎቹ በላሬና ኢታንግ ወረዳዎች በመኖሪያ ቤቶች፣ በጤናና በትምህርት ተቋማት ላይ የጎርፍ አደጋው ያደረሰውን ጉዳት መመልከታቸውም ተጠቅሷል።

የመስክ ምልከታው በሌሎችም ጉዳት በደረሰባቸው የክልሉ አካባቢዎች የሚቀጥል ሲሆን የስራ ሀላፊዎቹ ከመስክ ምልከታው በኋላ የመፍትሄ አቅጣጫ ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።  

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም