የደቡብ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች የጋራ ፎረም በጂንካ እየተካሄደ ነው

185

መስከረም 22 /2015 (ኢዜአ) የደቡብ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች የጋራ ፎረም “የምሁራን ተሳትፎ ለአገራዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ በጂንካ በመካሄድ ላይ ነው።

በጂንካ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት እየተከናወነ በሚገኘው ፎረም ላይ በክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራን፣ የደቡብ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ አባላት ተሳትፈዋል።

የወልቂጤ፣ ዲላ፣ ጂንካ፣ አርባምንጭ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ዋቸሞ እና የወራቤ ዩኒቨርሲቲዎች በፎረሙ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ምሁራኑ በጥናትና ምርምር ስራዎችና በመማር ማስተማር ስራዎች የልምድ ልውውጥና በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።