ተመራቂዎች ሙያዊ ግዴታቸውን መወጣት አለባቸው-- የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

141

ሀረር መስከረም 22/2015 (ኢዜአ) ሀገርን ለማገልገል ተመራቂዎች ሙያዊ ግዴታቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለጹ።

የሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ የጤና ሙያ ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 75 ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል።

በምርቃት ስነስረአቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ባስተላለፉት መልዕክት ኮሌጁ ለአገሪቱ በጤናው ዘርፍ የተማረ የሰው ሃይል በማፍራት እያበረከተ ያለው ሚና ከፈተኛ ነው።

May be an image of 1 person and indoor

ተመራቂዎች በሚሰማሩበት የስራ መስክ አገራቸውንና ህዝባቸውን በቅንነትና በታማኝነት በማገልገል ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ መልእክት አስተላልፈዋል።

በተለይ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች ሀገርን በመደገፉና በማሻገር ከፍተኛ ሃላፊነት ይጠበቅባቸዋል ያሉት አቶ ኦርዲን፤ ሙያዊ ስነ ምግባር በማክበር በቅንነት ማገልገል ይገባል ብለዋል።

የሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ አብዱሰመድ መሀመድ ኮሌጁ ለ46 ዓመታት ከጤና ረዳትነት እስከ መጀመርያ ድግሪ ድረስ በርካታ የጤና ባለሞያዎችን አስተምሮ አስመርቋል።

ኮሌጁ ዛሬ በክሊኒካል እና አዋላጅ ነርስ፣ በፋርማሲ፣ በራድዮግራፊና በሌሎች የጤና ሙያ ዘርፎች መሆኑ ተመላክቷል።

ኮሌጁ ለ27ኛ ዙር አሰልጥኖ ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል 374ቱ በመጀመርያ ድግሪ ሲሆኑ ቀሪዎቹ በደረጃ 4 የተመረቁ የጤና ባለሙያዎች መሆናቸውን የጠቀሱት የኮሌጁ ዲን ከተመራቂዎቹ መካከል 519 ኙ ሴቶች መሆናቸውንም ገልጸዋል።

የሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ1969 ዓ.ም ጤና ረዳት ሃኪሞችን ለማሰልጠን በህይወት ፋና ሆስፒታል መቋቋሙ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም