የሴካፋ የምድብ ድልድል ወጣ

158

መስከረም 22/2015 (ኢዜአ) በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከነገ ጀምሮ የሚካሄደው ከ17 አመት በታች የሴካፋ እግር ኳስ ውድድር የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ።

በዚሁ መሰረት በምድብ አንድ ኢትዮጵያ፣ሶማልያና ታንዛንያ፤ በምድብ ሁለት ዩጋንዳ፣ብሩንዲና ደቡብ ሱዳን ተደልድለዋል።

ነገ በውድድሩ መክፈቻ ዕለት ከቀኑ 7 ሰአት ዩጋንዳ ከብሩንዲ እንዲሁም ከቀኑ 10 ሰአት ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ይጫወታሉ።