የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

182

መስከረም 22 / 2015 (ኢዜአ) የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

ድጋፉን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ ለአባገዳዎች እና ለዞኑ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ባስረከቡበት ወቅት እንዳሉት የቦረና ዞን የውሃ ችግር በዘላቂነት እንዲፈታ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ ነው።

በዚህም በግንባታ ሂደት ላይ ያለውን የቦረና የውሃ ፕሮጀክት በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ይሰራል ሲሉ ተናግረዋል።

May be an image of 7 people, people standing and outdoors

የውሃ ፕሮጀክቱ ተጠናቆ የህዝብ ጥያቄ በመሰረታዊነት ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የዕለት ደራሽ ምግብ ማድረስ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የቦረና ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጃርሶ ቦሩ በዞኑ በድርቁ ሳቢያ ከ600 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው በመጠቆም ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

በመንግሥት በኩል ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የዕለት ደራሽ ዕርዳታ እየተደረገ መሆኑን ገልፀው፤ በበቂ ደረጃ እንዲደረስ ሌሎች አካላት ድጋፋቸውን ማጠናከር እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።