ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሶማሊያ ፕሬዚዳንትን ተሰናበቱ

143

መስከረም 20 / 2015 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድን ተሰናበቱ።

ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወቃል።

May be an image of 15 people, people standing and suit

በጉብኝቱም ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና የሶማሊያ አቻቸው ሀሰን ሼህ ሞሀመድ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን በተለይ በቀጠናው ሽብርተኝነትንና አክራሪነት በትብብር መዋጋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንዲሁም በሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ትብብር ላይ መወያየታቸው በወጣው የጋራ የአቋም መግለጫ ማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም