የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ)አመራሩን መረጠ

144
ጅማ መስከረም 11/2011 የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) 55 የማዕከላዊ ኮሚቴና ሥራ አስፈጻሚ አባላትን መረጠ። ኦዴፓ በጅማ እያደረገ ባለው ድርጅታዊ ጉባዔው 55 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን የመረጠ ሲሆንለኢህአዴግ ምክር ቤት አባልነትም 45 አባላትን መርጧል። በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ለመመረጥ የተጠቆሙት 60 እጩዎች ናቸው። ጉባኤው በሰጠው ድምጽ መሰረትም  ዶክተር አብይ አህመድን የድርጅቱ ሊቀመንበር፣ አቶ ለማ መገርሳን ደግሞ  በምክትል ሊቀመንበርነት  መርጧል። የፓርቲው ሊቀመንበር ዶክተር አብይ አህመድና ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፣ አቶ አዲሱ አረጋ፣አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ፣ አቶ ፍቃዱ ተሰማ፣ ወ/ሮ አዳነች አበቤ እና ዶክተር ዓለሙ ስሜ በስራ አስፈጻሚነት ተመርጠዋል። የማዕከላዊ ኮሚቴ ሆነው ከተመረጡት አባላት መካከልም ለኢህአዴግ ምክር ቤት አባልነት የተመረጡት፡-
  1. ዶክተር አብይ አህመድ
  2. አቶ ለማ መገርሳ
  3. ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ
  4. አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ
  5. ወይዘሮ አዳነች አቤቤ
  6. ኢንጂነር ታከለ ኡማ
  7. አቶ ሽመልስ አብዲሳ
  8. አቶ ኡመር ሁሴን
  9. ወይዘሮ ጠይባ ሀሰን
  10. አቶ አዲሱ አረጋ
  11. ዶክተር ግርማ አመንቴ
  12. ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ
  13. ዶክተር ሚልኬሳ ሚደጋ
  14. ዶክተር ተሾመ አዱኛ
  15. አቶ ታዬ ደንደአ
  16. ዶክተር አለሙ ስሜ
  17. ዶክተር ቶላ በሪሶ
  18. አቶ ደመላሽ ገብረሚካኤል
  19. አቶ ግርማ ሀይሉ
  20. አቶ ወርቁ ጋቸና
  21. አቶ ሻፊ ሁሴን
  22. አቶ ቶሎሳ ገደፋ
  23. አቶ ፍቃዱ ተሰማ
  24. አቶ ብርሃኑ በቀለ
  25. አቶ አወሉ አብዲ
  26. አቶ ጌቱ ወዬሳ
  27. አቶ ካሳሁን ጎፌ
  28. አቶ መላኩ ፈንታ
  29. አቶ ታረቀኝ ገለታ
  30. አቶ አበራ ወርቁ
  31. አቶ መኩዬ መሃመድ
  32. አቶ አህመድ ቱሳ
  33. አቶ አሰግድ ጌታቸው
  34. አቶ ደንጌ ብሩ
  35. አቶ ነመራ ቡሊ
  36. አቶ አብዱልአዚዝ መሃመድ
  37. አቶ ሮባ ቱርጬ
  38. አቶ ጀማል ከድር
  39. አቶ መሃመድ ከማል
40 . አቶ ከፍያለው ተፈራ
  1. አቶ መስፍን አሰፋ
  2. ወይዘሪት ሌሊሴ ለሚ
  3. አቶ ናስር ሁሴን
  4. አቶ ሞገስ ኢደኤ
  5. ዶክተር ደረጄ ዱጉማ በመሆን ተመርጠዋል።
የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) የሚለው ስያሜ፤ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦህዴድ/ በጅማ እያካሄደ ባለው 9ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ የቀድሞውን ስያሜ በመቀየሩ ነው። ፓርቲው ይወክለኛል የሚለውን ዓርማና መዝሙር በመለወጥ ማጽደቁም ይታወሳል። ድርጅቱ ለረጅም ጊዜ በተለያዩ የአመራርነት እርከን ያገለገሉትን  14 ነባር አመራር አባላትን በክብር ማሰናበቱም እንዲሁ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም