ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

646

መስከረም 17 /2015(ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ በማረፉ የተሰማኝ ኀዘን ከባድ ነው ብለዋል በሐዘን መልዕክታቸው።

ለሀገሩ በአጭር እድሜው ብዙ የሠራ ከያኒ ነው በማለት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሀገር በተደፈረች ጊዜ ሕመሙን እየቻለ ግንባር ተገኝቶ ሠራዊቱን አጀግኗል፣ ሠልጣኞችን አበርትቷል ሲሉ ለሀገር ያበረከተውን አስተዋጽኦ ዘክረዋል።

ነፍሱ በሰላም ትረፍ ብለዋል በሐዘን መልዕክታቸው።