የጅማ ዞን በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የተተከሉት ችግኞችን መንከባከብ ጀመረ

178

ጅማ፣ መስከረም 17/2015 (ኢዜአ) በአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ የታለመውን ውጥን እውን ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ቲጃኒ ናስር ገለጹ

በጅማ ዞን ማና ወረዳ ባለፋት አመታት የተተከኩሉ ችግኞችን የመንከባከብ ዘመቻና ችግኞቹ ያሉበትን ሁኔታ ተጎብኝቷል።

የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ቲጃኒ ናስር በችግኝ እንክብካቤ ዘመቻ ላይ እንዳሉት ችግኞችን በየአመቱ ከመትከል በተጓዳኝ የተተከሉ ችግኞችን ከአረም በማጽዳትና በመኮትኮት የመንከባከብ ስራ ለተጀመረው የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ትልቅ ትርጉም ያለው ነው።

''የምንተክላቸው የዛፍና የፍራፍሬ ችግኞች በተገቢው ሁኔታ ጥበቃና እንክብካቤ ካልተደረላቸው የተፈለገውን ውጤት ማምጣት አይችሉም'' ብለዋል።

ዞኑ ትኩረት ሰጥቶ የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንመ ተናግረዋል።

የጅማ ዞን ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መሀመድጣሀ አባ ፊጣ በበኩላቸው በዞኑ በዚህ አመት 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ችግኝ መተከሉን ጠቅሰው ችግኞችን የመንከባከብ እንቅስቃሴ መጀመሩን ተናግረዋል።

አቶ መሀመድ ጣሃ በዞኑ ከተተከሉ ችግኞች የጽድቀት መጠኑን የበለጠ ለማድረግ አየተሰራ ነው ብለዋል።

በተለይም በየአከረባቢው የተተከሉ ችግኞችን ከመከታተልና ከመንከባከብ ከንጻር ለነዋሪዎች፤ በባለሞያዎች የምክርና የግንዛቤ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የማና ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሰመሩዲን አህመድ እንዳሉት በወረዳው ተተክሉ ችግኞችን ህብረተሰቡን በማንቀሳቀስ የመንከባከብ ስራ አየተሰራ ነው ብለዋል።

''ችግኞች እንደ ህጻን ልጅ እንክብካቤ ይፈልጋሉ፤ ከተሰራባቸውና ከተጠበቁ ቶሎ ያድጋሉ፤ ስለዚህ የተከልኳቸውን እየተንከባከብኩ ነው'' ያሉት በችግኝ እንክብካቤ ዘመቻው ተሳታፊ የነበሩት አቶ ሱልጣን አህመድናቸው።

የዛፍም ሆነ የፍራፍሬ ተክሎች ከሚተከሉበት ቦታ ዝግጅት ጀምሮ ከተተከሉ ቦኋላ መኮትኮትና ውሃ ማጠጣትና ከተለያዩ አደጋዎች መጠበቅ ያስፈልጋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም