የመስቀል በዓልን ስናከብር ችግሮቻችንን በእርቅና ይቅርታ በመፍታት ሊሆን ይገባል-ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

206

መስከረም 16 /2015 (ኢዜአ) የመስቀል በዓልን ስናከብር ችግሮቻችንን በእርቅና ይቅርታ በመፍታት ሊሆን ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ተናገሩ።

May be an image of 4 people, people standing, fire and outdoors

ቅዱስነታቸው ይህንን ያሉት በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ እየተከበረ ባለው የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ነው።

በመልዕክታቸው የመስቀል በዓልን ስናከብር ችግሮቻችንን በእርቅና ይቅርታ በመፍታት ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

የሰው ልጅ ችግሮችን በሰላም እና በይቅርታ መፍታት ይችላል ያሉት ፓትርያርኩ ሰው ጠብን በዕርቅ ክህደትን በይቅርታ መሻር የሚችልበት አቅም እንዳለውም ገልጸዋል።

ነገረ መስቀሉን በውል የተረዳ ፍጡር ይቅርታ ተጠይቆ ቀርቶ ወደ በዳይ በመሄድ ጭምር ዕርቅን መፈጸም አያዳግትም ሲሉም አክለዋል።

በእግዚአብሄር አምሳል የተፈጠርን ሁሉ ለሰላም እና ለዕርቅ መሸነፍ የለብንም ያሉት ቅዱስነታቸው በዕርቅ ላይ የተመሰረተ የጠብ መፍትሄ በመንፈሳዊ፣ በዓለማዊ እና በሞራላዊ ህግጋት ሁሉ ተቀባይነት ያለው ነው ብለዋል።