ኢትዮ-ቴሌኮም የተቋሙን የቀጣይ ሶስት ዓመት የዕድገት ስትራቴጂ አስተዋወቀ

142

መስከረም 16 ቀን 2015(ኢዜአ) ኢትዮ-ቴሌኮም የተቋሙን የቀጣይ ሶስት ዓመት የዕድገት ስትራቴጂ አስተዋወቀ ፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የቀጣይ ሶስት ዓመት የዕድገት  ስትራቴጂ እና የ2015 በጀት ዓመት የስራ እቅዱን በዛሬው እለት አስተዋውቋል።

የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዚህን ወቅት ባለፉት ሶስት ዓመታት ተግባራዊ የነበረው የተቋሙ ስትራቴጂ  ተቋሙ ብቁ ፤ ተወዳዳሪና ተመራጭ የቴሌኮም ኦፕሬተር እንዲሆን መሠረት የጣለ መሆኑን ገልፀዋል።

በሶስት ዓመት ውስጥ የደንበኞችን ቁጥር 37 ሚሊዮን ወደ 66 ሚሊዮን በማሳደግ በ75 በመቶ እንዲጨምር አድርጓል ነው ያሉት፡፡

ከገቢ አንጻርም 76 በመቶ እድገት እንዲመዘገብ ማድረጉን ጠቅሰዋል፡፡

“ሊድ”  የተሰኘው የኢትዮ ቴሌኮም አዲሱ የሶስት ዓመት ስትራቴጂ ከሐምሌ 2014ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

ስትራቴጂው በቀጣይ ሶስት ዓመት አስተማማኝ የኮሙዩኒኬሽን እና የዲጅታል ፋይናንስ አገልግሎት በማቅረብ የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማፍጠን ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በቴሌኮም ገበያ ከፍተኛ ድርሻ በመያዝ የአገልግሎት ተደራሽነትና እርካታን ለማሳደግ እንደሚሰራም እንዲሁ፡፡