ዛሬ ከምንም ነገር በላይ ለእውነት የምንቆምበት ጊዜ ነው -የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር

207

መስከረም 16 ቀን 2015(ኢዜአ) በዙሪያችን ብዙ የተሳሳቱ መረጃዎች እና ከፋፋይ አስተሳሰቦች በመበራከታቸው ዛሬ ከምንም ነገር በላይ ለእውነት የምንቆምበት ጊዜ ነው ሲሉ የድቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ተናገሩ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ለመስቀል ደመራ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምክትል ርዕሰ-መስተዳድሩ በመልዕክታቸው የደመራና መስቀል በዓልን ስናከብር አካባቢያችንን ለጥፋት ከተሰለፉ ሰርጎ ገቦች በመጠበቅ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

እያንዳንዱ ጭራሮ ተደምሮ ችቦ፤ እያንዳንዱ እንጨት ተሰብስቦ ደግሞ ደመራን እንደሚሠራው ሁሉ በእኛ አንድነት ሀገራችን የደመራ ምሳሌ ናት፤ እንደ ደመራው ሁሉ አንድ ሆነን ከፊታችን ያለውን የተስፋ ቀን በጉጉት ልንጠባበቅ ይገባናል ሲሉም ተናግረዋል፡፡