በዓሉ ለክልሉ ህዝብና ለመላ ኢትዮጵያውያን የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነትና የመተሳሰብ እንዲሆን እመኛለው- የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

107

መስከረም 16 ቀን 2015(ኢዜአ) የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኡሞድ ኡጁሉ እንዳሉት ህዝበ ክርስትያኑ የመስቀል በዓል አከባበር እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር በማድረግ የተቸገሩ ወገኖችን በማብላትና የተጠሙትን በማጠጣት ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ የተለመደ የመተዛዘንና የመረዳዳት ባህሉን በመተግበር በዓሉን ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር እንዲያከብር ጥሪ አቅርበዋል።

የተጀመረው የእድገት እና የብልጽግና ጉዞ እውን እንዲሆን በየአካባቢያችን ሰላማችንን አጽንተን ያሉንን ጸጋዎች በመጠቀም ሙሉ አቅማችንን እና ትኩረታችንን በልማት ላይ ልናደርግ ይገባል ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።

መስቀል በሁሉም አካባቢዎች የሰላም፣ የአብሮነት፣ የመተሳሰብ፣ የመደጋገፍ፣ የመከባበር እንዲሁም የተጣሉ ይቅር የሚባባሉበት እሴታችን ደምቆ የሚታይበት በዓል እንደሆነ አውስተዋል።

ህዝቡ ከሁሉም በላይ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር መስዋዕትነት እየከፈሉ ያሉ ጀግኖችን በማሰብ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ ማቅረባቸውን ከጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙንኬሽን ጉዳዩች ጽህፈት ቤት

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም