በስራ ፈጠራ ዘርፍ አዲስ እሳቤን መሠረት ያደረገና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ውይይት በአሶሳ እየተካሄደ ነው

180

አሶሳ ኢዜአ (መስከረም 15/2015 ዓ.ም.) በስራ ፈጠራ ዘርፍ አዲስ እሳቤን መሠረት ያደረጉ እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ውይይት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ውይይቱ በስራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን እየተመራ ይገኛል።

የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ባለፉት ጊዜያት በስራ እድል ፈጠራ የተከናወኑ ጉዳዮችን በማቅረብ ላይ ናቸው።

በስራ ፈጠራ ዘርፍ አዲስ እሳቤን መሠረት ያደረጉ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች አስመልክቶ ለውይይት መነሻ ሃሳብ እያቀረቡም ነው።

ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት እንዳሉት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በማዕድን፣ ግብርና እና ቱሪዝም ዘርፍ እምቅ ሃብት አለው።

ውይይቱ ሚኒስቴሩ ከክልሉ መንግስት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ለማጠናከር ያለመ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

በውይይቱ የቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰንን ጨምሮ የፌደራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም