ኢትዮጵያና ሱዳን ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ

275

መስከረም 16 ቀን 2015 (ኢዜአ) ኢትዮጵያና ሱዳን ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታቸውን ዛሬ ከቀኑ 10 ሰአት በአበበ በቂላ ስታዲየም ያደርጋሉ።

ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች 13 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ ጨዋታ 1 ለ 1 አቻ መለያየታቸው የሚታወስ ነው።

በጨዋታው ለግብጹ ኤል-ጉና ክለብ የሚጫወተው ሽመልስ በቀለ ለዋልያዎቹ አብዱልራዚቅ ያኩብ ለሱዳን ግቦቹን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስፖርቱ ቤተሰቡ ጨዋታውን በነጻ በመታደም ብሔራዊ ቡድኑን እንዲያበረታታ ጥሪውን አቅርቧል።

በፊፋ ወርሃዊ የአገራት የእግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ 138ኛ፤ ሱዳን ደግሞ 130ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።