የጋሞ ብሔር የዘመን መለወጫ “ዮ..ማስቃላ” በዓል በአርባምንጭ ከተማ እየተከበረ ነው

213

አርባምንጭ መስከረም 14 ቀን 2015 (ኢዜአ) የጋሞ ብሔር የዘመን መለወጫ “ዮ..ማስቃላ” በዓል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በተለያዩ መርሃ ግብሮች በአርባምንጭ ከተማ እየተከበረ ነው፡፡

የዓሉ አከባበር በጋሞ ዞን አስተዳደር ግቢ በተገነባው የጋሞ ብሔር የሰላም ተምሳሌት ምልክት ሀውልት ምረቃ ተጀምሯል፡፡

የጋሞ የጥበብ ሥራዎች እንድሁም ህዝቡ በደስታና በሀዘን ጊዜ የምጠቀሟቸው ባህላዊ ቁሳቁሶች በጋሞ ዞን ባህል ማዕከል በኤግዚቢሽንነት ቀርቦ ታዳሚዎች እየተመለከቱ ይገኛሉ፡፡

ከ”ዮ ማስቃላ” በዓል ጋር በተያያዘ በተደረጉ ጥናታዊ ጽሁፎች ፓናል ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡

በዓሉ ላይ የፌደራል የመንግስት ተጠሪ አቶ ተስፋዬ በልጅጌን ጨምሮ የፌደራል፣ ክልሎች፣ የዞኖችና የልዩ ወረዳዎች የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ታድመዋል።

ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የመጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ሀይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎችና ሀደ ስንቄዎች፣ አርቲስቶችና እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶችም ተገኝተዋል፡፡