“ህዝብ ነው ሀይላችን” እያለ በዜጎች ሞት የስልጣን ዕድሜን ለማራዘም የተቀረጸ ክልላዊ መዝሙር

202

ምክንያታዊ ባልሆነ የዜጎች ሞት የስልጣን ዕድሜን ለማራዘም ሲባል በተቀረጸ ክልላዊ መዝሙር ሁሉም ሊያስቆመው ይገባል፡፡

የትግራይ ወጣቶች ባለፉት በርካታ ዓመታት የህወሃት የሽብር ቡድን በሚበክለው የፖለቲካ መርዝ አዳዲስ አስተሳሰቦችን እንዳያፈልቁ፣ተራማጅ የፖለቲካ አስተሳሰብን እንዳይከተሉ ያደረገ ነው።

አሸባሪው ህወሃት ፍላጉቱን ለማሳካት ባለፉት በርካታ ዓመታት ክልላዊ መዝሙሩን በሚፈልገው መንገድ በመቅረጽና ጥቅም ላይ በማዋል ምንም አይነት አዳዲስ የፖለቲካ አመለካከት እንዳይራመድ ክልከላ በመጣል ህዝቡ ሁሌም ስለወረራና ጦርነት በመስበክ በስጋት እንዲወጠር ማድረግን፣ ከሌሎች የኢትዮጵያ እህት ወንድሞቹ ጋር በጋራ እንዳይኖር ጥርጣሬ እንዲያድርበት ማድረግን፣ ህገ-ወጥ ምርጫ ማካሄድን እና መሰል ስልቶችን ሲጠቀም መቆየቱ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ 

ይህ የሽብር ቡድን የትግራይ ህዝብ በተለይ ወጣቱ የማህበረሰብ ክፍል ከጦርነት ውጪ የተሻለ ማሰብ እንዳይችል የሚያደርጉ በርካታ የሴራ ፖለቲካ ተግባራትን ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ከእነዚህ ተግባራት መካከል አንዱና ዋነኛው የክልሉን መዝሙር የቀረጸበት መንገድ ይጠቀሳል፡፡

በመደረ ላይ “ህዝብ ነው ሀይላችን”  እያለ ህዝብ የሚያስፈጅና ወደጦርነት እየማገደ የሚኖር ብቸኛ አምባገነን ቡድን አለ ከተባለ አሸባሪው ህወሃት ነው፡፡ ቡድኑ ለበርካታ ዓመታት ህዝቡ በፍርሃት ተሸብቦ እንዲኖር፣ አዳዲስ የፖለቲካም ሆነ የፈጠራ ሃሳቦች እንዳይፈልቁ እንደመሳሪያ ሲጠቀምበት የነበረው የመዝሙር ክፍሎችን እንደሚከተለው እንመልከት፤

…“በጸሀይ ሀሩርና በቁር፣ ነፍሳችን ውሃ ይጥማት፣

ዓለት ይሁን ትራሳችን ዋሻ ይሁን ቤታችን፣

ሌትም ቀንም ጉዞ ይድከመንም ይራበንም፤…

…በጅቦች እንከበብ፣ መሬት ይጥበበን፣

የጠላተቻችን ጥርስ ስጋችን ውስጥ ይቀርቀር፣

ስጋችን ላሞራ፣ ደማችን እንደጎርፍ ይፍሰስ፣

አጥንታችን ይድቀቅ፣ ዱቄት ሆኖ ይበተን፤…

…የጦር መሳሪያ መርዝ፣ ፋሽስታዊ ንዳድ፣

ሚሊዮን ጠላቶቻችን ፊታችን ላይ ይጉረፉ፣

መስዋዕትነት መቁሰልና ኪሳራም እንከፍላለን፣

የከፋ መከራም ቢመጣ ወደን እንከፍላለን፤…”

በሚሉ ከጦርነት ውጪ ለወጣቶች ተስፋ በማያሳዩ፤ ቃላት የክልሉን መዝሙር መቀንበቡ፤ በዚህ ውስጥም የራሱን ፖለቲካዊ ጥቅም ሲያስጠብቅ መቆየቱን ማየት ይቻላል፡፡

ላለፉት 45 እና ከዛ በላይ ለሆኑ ዓመታት የከፋፍለህ ግዛ ስልትን ሲጠቀም የቆየው የህወሃት የሽብር ቡድን በሀገርና በህዝብ ላይ የፈጸማቸው እኩይ ተግባራቱ በፋሽስትነት የሚያስፈርጀው ቢሆንም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ተጽዕኖ ማሳረፍና ተጠያቂ አለማድረጉን የዘርፉ ምሁራንና ተንታኞች ደጋግመው ገልጸዋል፡፡

በክልላዊ መዝሙር ላይ የተቀመጡት መልዕክቶች በሙሉ ሀገራዊ አመለካከት እንዲኮሰምን፣ የቡድኑ ስልጣን ዘላቂ የሚሆነው በዜጎች ሞት እና እንግልት እንደሆነ በግልጽ ያስቀምጣል፡፡

የክልሉ ተወላጅ ተማሪዎች የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን ስኬታማ እንዲሆን በሳይንሳዊ ምርምርና የፈጠራ ስራዎች ላይ ማተኮር እንዳይችሉ የሚያደርጉ መልዕክቶችን በመቅረጽ ነጋ ጠባ እንዲዘምሩት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

ይህ የሽብር ቡድን ለዓፉ ህብረ-ብሔራዊ /ፌዴራሊስት/ ነኝ ይበል እንጂ ፈጽሞ ህዝብን ማስተዳደር በማይችልበት ፖለቲካዊና ሰብዓዊ ውድቀት ላይ እንደሚገኝ የመረጃ ምንጮቻችን በየጊዜው የሚያደርሱን መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡

የቡድኑ ድብቅ ፍላጎቱ ምን እንደሆነ ባለፉት ጊዜያት በብሔርና ብሔረሰቦች ስም እንዴት እንደነገደ፣ ሀገር እንደ ሀገር እንዳትቆም ምን ሲሰራ እንደነበር፤ ሀገር አሁን ለገጠማት ችግር ዋና ምክንያቱ እንደሆነ፤ የከፋፍለህ ግዛ አስተሳሰቡን ለመተግበርና በብሔር ብሔረሰቦች ስም የስልጣን ዘመኑን እንዴት እንዳራዘመ ያለፉት ዕኩይ የፖለቲካ ሴራዎቹ ግልጽ አድርገው ያሳያሉ፡፡

ለዚህም ትክክለኛ ተግባሩ ህያው ምስክር ነው፡፡ የሽብር ቡድኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተፈጸሙ የሽብር ተግባራትም ሆነ /በፋሽስትነት/ የሚያስፈርጁ በርካታ የዘር ጭፍጨፋዎች መፈጸሙን በአማራ እና በአፋር ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች የፈጸማቸው እና በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች በተልዕኮ ያስፈጸማቸው የሽብር ተግባራቱ ህያው ምስክሮች ናቸው፡፡

ይህ የሽብር ቡድን ለከፍተኛ ሰቆቃ በመዳረግ የትግራይ ህዝብ በሰላም የመኖር መብቱን ከመግፈፉ በተጨማሪ ያልተገባ የህይወት መስዋዕትነት እንዲከፍል እያደረገውም ይገኛል፡፡

የቡድኑን ዕኩይ ሴራ በውል የተገነዘቡ የትግራይ ወጣቶች የዕኩይ ተግባሩ ተሳታፊ አንሆንም በማለታቸው ብቻ ለአፈሳ እና ለአፈና እየተዳረጉ መሆናቸውን በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የመረጃ ምንጮቻችን ያጋሩን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

የሽብር ቡድኑን አፈሳ እና አፈና በመሸሽ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዲሸሹ እያደረጉ መሆናቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።

የሽብር ቡድኑ በክልሉ ተወላጆች ላይ ካደረሰው ሰቆቃ በተጨማሪ በእብሪት በወረራቸውና ጭፍጨፋ በፈጸመባቸው አካባቢዎች በማህበረሰብ ላይ የህይወት ህልፈት፣ የንብረት ውድመት፣ የስነ-ልቦና ጫና ማድረሱ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡

ቡድኑ እቆረቆርለታለሁ ብሎ ለይስሙላም ቢሆን የሚናገርለትን ህዝብ ማእበል አግተልትሎ በጦርነት በመማገድ ፋሽስታዊ መገለጫውን በአደባባይ አውጥቶ አሳይቷል፡፡

የሽብር ቡድኑ በየቀኑ በሚፈጥረው የሀሰት ትርክት የትግራይን ህዝብ ዙሪያህን ጠላት ከቦሃል፤ ተነስ እያለ በግዳጅ የእሳት እራት እያደረገው ይገኛል፡፡

"የትግራይ ከፍታ የሚረጋገጠው በኢትዮጵያ መቃብር ላይ ነው" በሚል የእናት ጡት ነካሽ ባህሪው በመነሳሳት የሰላም አማራጭ ቢቀርብለትም ጦርነትን ምርጫው በማድረግ የአለም ህግጋትን በመጣስ ጭምር ወደ ጦርነት የማገዳቸው ታዳጉ ልጆች “ለሽብር ቡድኑ አላማ መሰለፍ ከንቱ በመሆኑ እጃችንን ሰጥተናል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ቡድኑ ከኢትዮጵያዊ ስነ ልቦና እጅጉን የራቀና የክፋት መንፈስ የተጠናወተው በመሆኑ፤ የሚከተለው ፅንፍ የወጣ ብሄርተኝነትና በአጉል ጀብደኝነት በተሞላ ጦረኛ አባዜው ምክንያት የትግራይ ህዝብ በየቀኑ ሊገመት የማይችል ያልተገባ የህይወት፣ የአካል፣ ቁሳዊና ስነ ልቦናዊ ዋጋ እየከፈለ እንደሚገኝ በክልሉ የሚገኙ የመረጃ ምንጮቻችን ገልጸውልናል፡፡

ይህ እኩይ ተግባሩ የሚያበቃው እና የትግራይ ህዝብ ሰቆቃ የሚያቆመው ይህ የሽብር ቡድን እና እሱ የተከለው መርዝ ከስሩ ሲነቀል መሆኑን በርካቶች ይስማሙበታል፡፡

የሽብር ቡድኑ በትግራይ ህዝብ መሃል ቢሸሸግም እንዳሻቸው የሚዘውሩት የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች እንደሁኑ የሚታወቅ ነው፡፡ የትግራይ ወጣት የጋላቢዎቹን ሴራ ለመፈጸም የሚሯሯጡትን የሽብር ቡድኑን መሪዎች ሀገር እኩይ ፍላጎት ለማሳካት ብቻ መሆኑን በውል ሊገነዘቡት እንደሚገባ የዘርፉ ተመራማሪዎች ይገልጻሉ፡፡

የኢትዮጵያውያን የመልማት እና ተጠቃሚነት የሚረጋገጠው በጋራ በመቆም  መሆኑን የትግራይ ህዝብ በውል ይገነዘባል፡፡ለዚህም ነው እህት ወንድሞቹም እንደወትሮው ሁሉ አስፈላጊውን እገዛና ድጋፍ እያደረጉለት የሚገኙት፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም