በ133 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተቋቋመው የጀብዱ ሞተርስ አክስዮን ማኅበር ፋብሪካ ተመረቀ

163

መስከረም 03 ቀን 2015(ኢዜአ) በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ በ133 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተቋቋመው የጀብዱ ሞተርስ አክስዮን ማኅበር ፋብሪካ ተመረቀ።

በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሽመልስ አብዲሳ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

ከፋብሪካው ምርቃት መርሐግብር በተጨማሪ ለአርሶ አደሮች በፋብሪካው የተገጣጠሙ ከ16ሺህ በላይ የውሀ መሳቢያ ፓምፖች ርክክብ የሚደረግ ይሆናል ።

May be an image of outdoors

የፋብሪካው ስራ መጀመር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ፣ ለስራ እድል ፈጠራና ከውጭ የሚገቡ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት እንደሚያግዝ ተጠቁሟል።

ለተጠቃሚዎች የሚተላለፉት የውሀ ፓምፖችም 75 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት የሚያግዙ መሆናቸው ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም