ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋሩ

161

አዲስ አበባ መስከረም 1 /2015 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋርተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና ቀደማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፤ የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋርተዋል። 

ለቂርቆስ፤ ልደታና አራዳ ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ አረጋዊያንና አቅመ ደካሞች ነው የምሳ ግብዣ ያደረጉት።

 ጠቅላይ ሚኒስትርሩ ለእንግዶቹ ካደረጉት የማእድ ማጋራት በተጨማሪ የበዓል ስጦታም በማበርከት ለሁሉም መልካም በዓል እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።

ከማዕድ ተጋሪዎች መካከል ኢዜአ ያነጋገራቸው ታዳሚዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰውና አክበረው ላደረጉላቸው ግብዣ አመስግነዋል። 

ሁሉም ወገን በዓሉን ከአቅመ ደካሞች ጋር በመጋራት ቢያከብር መልካም መሆኑን ጠቅሰው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተግባር ከግብዣም ባለፈ ታላቅ መልእክት አለው ብለዋል። 

በአዲሱ ዓመት ኢትዮጵያ የገጠማት ፈተና ሁሉ ተወግዶ ሰላም፣ ፍቅርና አንድነት ይሰፍን ዘንድ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም