9ኛው የኦህዴድ ድርጅታዊ ጉባኤ ተጀመረ

55
አዲስ አበባ መስከረም 9/2011 9ኛው የኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ድርጅታዊ ጉባኤ በጅማ ከተማ መካሄድ ጀምሯል። በጉባኤው ላይ የድርጅቱ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ 1 ሺህ 316 በላይ ተሳታፊዎች የታደሙበት ነው። ከነዚህ ውስጥ 1 ሺህ 66 በድምጽ ሰጪነት፣ 250ዎቹ በታዛቢነት እየተሳተፉ ነው ። ጉባኤው ያለፉ ሶስት ዓመታትን ጉዞና አፈጻጸም እንዲሁም የኦዲት ቁጥጥር ሪፖርት ላይ ውይይት እንደሚደረግም ይጠበቃል። የድርጅቱ ስያሜና መለያ ዓርማ እንዲሁም መዝሙር እንደሚለወጥም ተነግሯል። ድርጅቱ የደረሰበትን የትግል ደረጃ ያስቀጥላሉ የተባሉ አመራሮች ምርጫ እንደሚካሄድም አክለዋል። ዛሬ በይፋ የተጀመረው የድርጅቱ ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናትይካሄዳል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም