በሐረሪ ክልል ከተለያዩ ወረዳዎች ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው

160

ነሐሴ 29 ቀን 2014 (ኢዜአ) የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ በክልሉ ከተለያዩ ወረዳዎች ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ እየተወያየ ነው።

የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ እንደገለጹት አሸባሪው ህወሓት የመንግስትን የሠላም አማራጭ በመግፋት ለሶስተኛ ጊዜ ጦርነት ከፍቷል።

መንግስት የሰላም አማራጩን ያስቀመጠው ለሰላም በሰጠው ትኩረት ነው ያሉት ሃላፊው፤አሸባሪው የህወሃት ቡድን በአገሪቱ ላይ የከፈተው የውክልና ጦርነት መሆኑን ገልፀዋል።

በመሆኑም ይህን በመረዳት ወጣቱ መንግስት ለሚያደርጋቸው ዘርፈ ብዙ ጥረቶች አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የሀረሪ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ አብዱልሀኪም ኡመር መንግስት ለጥቂት ግለሰቦች የስልጣን ጥም ሲባል አገር እንዳትፈርስ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን እና አሁንም እንደሚቀጥልበት ተናግረዋል።

ምክትል ሃላፊው አክለውም አሸባሪው ህወሓት የከፈተውን ጦርነት የመከላከያ ሠራዊትና ሌሎች የጸጥታ አካላት በብቃት እየመከቱ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም