በአርባምንጭ ከተማ የተከሰተው ሁከት በቁጥጥር ስር መዋሉን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ

93
አርባምንጭ መስከረም 8/2011 በአዲስ አባበ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን  ቡራዩ አካባቢ  የተፈጸመውን ግድያ ለመቃወም በአርባምንጭ ከተማ የተካሄደውን ሰልፍ ተከትሎ የተፈጠረው ሁከት በጸጥታ ኃይሉ ቁጥጥር ስር መዋሉን የጋሞ ጎፋ ዞን አስተዳደር አስታወቀ። ተፈጠረውን ሁከትና መረጋጋቱን አስመልከቶ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኢሳያስ እንድሪስ ለጋዜጠኞች  በሰጡት መግለጫ  አዲስ አበባ ዙሪያ ቡራ አካባቢ  በዞኑ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ግድያ ለመቃወም የተካሄደው ሰልፍ ወደ ሁከት ተቀይሮ ጉዳት ደርሷል። ጥቂት "ሰልፉን ለማወክ በሞከሩና በጸጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ለጊዜው የሁለት ሰው ህይወት ማለፉንና በ13 ሰው ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል። ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር ባይተባበር ጉዳቱ ከዚህም የከፋ ሊሆን ይችል እንደነበረ የገለጹት አቶ ኢሳያስ ከተማውን ለማረጋጋት ህብረተሰቡ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመሆን ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል። በከተማው የተፈጠረው አለመረጋጋት ሙሉ በሙሉ በጸጥታ ኃይሉ ቁጥጥር ስር መዋሉንና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳትም በመጣራት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም