የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተጀመረ

85
ሀዋሳ ግንቦት 11/2010 የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ዛሬ በሀዋሳ ተጀመረ። ማዕከላዊ ኮሚቴው በስብሰባው በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ተግባራትን ከተቀመጠላቸው የትኩረት አቅጣጫ አንጻር ያላቸውን አፈጻጸም በጥልቀት ይገመግማል፡፡ በቆይታው በክልሉ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲ ስርዓት እንዲሁም  በልማት ሰራዊት ግንባታ ሂደት ላይ የነበሩ ጥንካሬና ድክመቶችን ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣል፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ ድርጅታዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ በመወያየት ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም