አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ውክልና ሊኖራት ይገባል -የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ

91

ነሐሴ 13 ቀን 2014 (ኢዜአ) አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ውክልና ሊኖራት ይገባል ሲሉ የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ተናገሩ።

በሕዳር 2021 በዳካር የተካሄደውን 8ኛው የቻይና አፍሪካ የትብብር ፎረም ውሳኔዎች አተገባበር የሚከታተለው የአስተባባሪዎች ስብሰባ ትናንት በበይነ መረብ ተካሂዷል።

ስብሰባውን የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ እና የሴኔጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አይሳታ ቶል ሳል በጋራ የመሩት ሲሆን የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ የተመድ ጸጥታ ምክር ቤትን ጨምሮ የአፍሪካ ውክልና እንዲሰፋ ቻይና አስተዋጽኦ ታደርጋለች ብለዋል።

በተጨማሪም በደቡብ- ደቡብ ትብብር መርህ የአፍሪካ መሰረት ልማት እና አብሮ የማደግ መርህን በተጠናከረ መልኩ አገራቸው እንደምትደግፍም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው ከዓለም ህዝብ 2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ወይም 21 ከመቶ የያዘው የቻይና ህዝብና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 28 በመቶ የያዙት አፍሪካውያን መካከል የሚደረገው ትብብር ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመዋል።

May be an image of 1 person

በሁለቱ መካከል ያለው ትብብር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ያሉት አቶ ደመቀ በርካታ የአፍሪካ አገራት ከቻይና ብድር የወሰዱ መሆኑን በመጠቆም በቀጣይ በሁለቱ አካላት መካከል ያለው ሂደት የብድር ጫናን በሚቀንሱ ድርድሮች ዙሪያ ተጨባጭ ውጤት እንዲያመጣ ጠይቀዋል፡፡

እንዲሁም ኢትዮጵያ በድህረ ኮቪድ በያዘችው የልማት ዕቅድ ዙሪያ ቻይና በቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እና ንግድ ድጋፏ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ቻይና በአፍሪካ ቀንድ ሰላም ፣መረጋጋት እና ልማት እንዲመጣ ትኩረት ሰጥታ መስራቷ የሚደነቅ ተግባር መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም