የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፕሬዝዳንት እና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የመጨረሻ እጩ ተወዳዳሪዎችን ዝርዝር ይፋ አደረገ

709

ነሐሴ 13 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፕሬዝዳንት እና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የመጨረሻ እጩ ተወዳዳሪዎችን ዝርዝር ዛሬ ይፋ አድርጓል።

ዝርዝሩ የወጣው በምርጫ አስፈጻሚ እና በይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ከታየ በኋላ መሆኑን ፌዴሬሽኑ ገልጿል።

በዚሁ መሰረት ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ሶስት እጩዎች እንዲሁም ለስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት 32 እጩዎች ተካተዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና የጋምቤላ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት እጩዎች ላይ ያቀረቡት ቅሬታ በይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው ምላሽ አግኝቶ ከሁለቱ ክልሎች በተመሳሳይ ሶስት እጩዎች እንዲካተቱ ተደርጓል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤